free book gift

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።


Iqra

=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=

ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ


1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።

2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።

3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።

4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
Iqra
Iqra

Homeየወጣቱ ተልዕኮ ምንነትየአቂዳ ትምህርቶችየሶላት መመሪያረመዷንሙስሊም ሴቶችኢስላማዊ ቤተሰብከታሪክ ማህደርሐዲስለወጣቶችትምህርትና መሰረታዊ ክህሎታችጤናችንግጥምጥያቄና መልስኢስላማዊ መዝገበ ቃላት
free book gift

=<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=

ያ ሁሉን በፈጠረው ጌታህ ስም አንብብ!

free book gift

በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው።

free book gift

:☀:♥ቁርአንና ቱርፋቱ♥:☀:


Let us deliver the messege of the Quran 1

በአሏህ ስም እጅግ በጣም እርህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው። የአሏህ ሰላምና እዝነት በረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ፣ በቤተሰቦቻቸው ፣ በሰሃቦቻቸውና የሳቸውን ፈለግ እስከ የውመልቂያማ ድረስ በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን።


-<({አል-ቁርአን 25:30-31})>-


(30) መልዕክተኛው(ሙሐመድ) ጌታየ ሆይ! ህዝቦቼ ይህን ቁርአን የተተወ ነገር አድርገው ያዙት(ችላ አሉት) አለ።

(31) እንደዚሁም ለነብያቶች ከሙጅሪሞች(ከአመፀኞች) የሆነ ጠላትን አድርገናል። መሪና ረዳትም በጌታህ በቃ።


1) በቡሐሪ እንደተዘገበው
የአሏህ መልዕክተኛ(ሰ.ዐ.ወ): ከናንተ መካከል በላጩ ቁርአንን ተምሮ ያስተማረ ነው ብለዋል።

2) እንዲሁም በሙስሊም እንደተዘገበው
የአሏህ መልዕክተኛ(ሰ.ዐ.ወ): ከሃያሉ አሏህ መጽሐፍ ሁለት አንቀፆችን ልታነቡና ልትማሩ አንዳችሁም ወደ መስጅድ አትሄዱምን? ለሱም ከሁለት ግመሎች በላይ ባላጮች ናቸው። ሶስት አንቀፆች ከሶስት ግመሎች በላይ በላጮች ናቸው። አራት አንቀፆች ከአራት ግመሎች በላይ በላጮች ናቸው....... ብለዋል።

3) በቡሐሪና ሙስሊም እንደተዘገበው
ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ): ቅናት በሁለት ነገሮች ዙርያ ካልሆነ በቀር ተቀባይነት የለውም። አሏህ ቁርአኑን የሰጠውና ከሱም ቀንም ማታም የቀራ ሰው። አሏህ ሃብትን(ገንዘብን) የሰጠውና በቀን በሌሊትም ከሱ የሰጠ የሆነ ሰው ሲቀር ብለዋል።

4) በቡሐሪና በሙስሊም
የአሏህ መልዕክተኛ(ሰ.ዐ.ወ): ከአሏህ መፅሐፍ አንድ ፊደል ያነበበ ሰው አንድ ሃሰና ያገኛል። ሃሰናው በአስር ይባዛል። <አሊፍ ላም ሚም> አንድ ቃል ነው አላልኩም። አሊፍ አንድ ፊደል ነው ላም አንድ ፊደል ነው ሚም አንድ ፊደል ነው ብለዋል።

5) በትርሚዚይ እንደተዘገበው
ረሱል(ሰ.ዐ.ወ): በእርግጥ በልቡ ምንም ቁርአን የሌለው(የማያውቅ ሰው) ልክ እንደ ጠፋ(እንደወደመ) ቤት ነው ብለዋል።

6) በትርሚዚይ እደተዘገበው
ቁርአን ለሚያነቡትና በክብር ለሚይዙት በየውመልቂያማ አማላጅ ይሆናል።

7) በሙስሊም እንደተዘገበው
የአሏህ መልዕክተኛ(ሰ.ዐ.ወ): ቁርአንን አንቡብ በትንሳኤው ቀን ለአንባቢዎቹ አማላጅ ሆኖ ይመጣልና ብለዋል።

8) በአህመድና በጦበራኒ እንደተመዘገበው
ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ፆምና ቁርአን በትንሳኤው ቀን ለአሏህ ባሪያ ያማልዳሉ። ፆምም ይላል ጌታ የሆይ! ከምግብና ከፍላጎቶቹ ከልክየዋለሁ፤ እናም ምልጃየን ተቀበለኝ ይላል። ቁርአንም በምሽት ጊዜ ከእንቅልፍ ከልክየዋለሁ፤ ለሱም ምልጃየን ተቀበለኝ ይላል። እንዲያማልዱም ይፈቀድላቸዋል ብለዋል።

9) በሙስሊም እንደተዘገበው የአሏህ መልዕክተኛ(ሰ.ዐ.ወ): በእርግጥ በዚህ መጽሐፍ(በቁርአን) አሏህ ህዝቦችን ከፍ ያደርጋል፤ በሱም ሌሎችን ዝቅ ያደርጋል(ያጠፋል) ብለዋል።

10) በቡሐሪና ሙስሊም እንደተዘገበው
የአሏህ መልዕክተኛ(ሰ.ዐ.ወ): ቁርአን የሚያነብ አማኝ ሰው ምስያው ልክ እንደ ትርንጐ ነው። ጣዕሙ ጣፋጭ ነው፤ ማዕዛውም አስደሳች ነው፤ ቁርአን የማያነብ አማኝ ደግሞ ምስያው ልክ እንደተምር ሲሆን ጣዕሙ ጣፋጭ ነው። ነገር ግን ማዓዛ(ሽታ) የለውም። ቁርአን የሚያነብ ሙናፊቅ ምስያው ልክ እንደ አሩቲ ነው። ሽታው አስደሳች ነው። ሆኖም ጣዕሙ መራራ ነው። እንዲሁም ቁርአን የማያነብ ሙናፊቅ ምስያው ልክ እንደ እንቧይ ሲሆን ጣዕሙ መራራ ነው። ሽታ የለውም ብለዋል።

[] Like the page
[] and share it with your friends
page:
http://facebook.com/youth.mission29


573

የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
free book gift

Download Islamic Books
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ

Important Web Links


free book gift

free book gift

free book gift

ስለወጣቱ ተልዕኮ ምንነት ለማወቅ እዚህ ላይ ክሊክ ያድርጉ

Copyright©Youth-Mission የወጣቱ ተልዕኮ


Ring ring